Sew Mehonne
Lyrics
እስቲ ልነሳና ልያዘው መንገዴን ♪ መውደድን ፍለጋ ስደተኛውን ♪ ለመንገደኛ ሰው አይነፍጉም ስንቁን ናፍቆት እንዳይበላው አንጀት አንጀቱን ♪ የማይጠፋ የሚጠፋብኝ ♪ የማይከፋው የሚከፋብኝ ♪ የማይቸግር የሚቸግረኝ ♪ የሚሆነው የማይሆንልኝ አሀሀሀሀ አወይ ሰው መሆኔ ♪ የማይመች የሚመቸኝ ♪ ያልበላሁት የሚያጠግበኝ ♪ ያለበስኩት የሚሞቀኝ ♪ በዕለተ ጀምበር የሚያስደስተኝ አሀሀሀሀ መውደድ ሲይዘኝ ♪ የፍቅር ቁስሉ የማይሽርልኝ ♪ ዞሮ መቃጠሉን የማይሆንልኝ ♪ ስቀርብም ስወድም እየጠረጠርኩኝ አሀ አሄሄ አሀ አሀሀ ኦሆይ አሄሄይ እምህ አሀሀ አማርረውና አምላኬን በፀና ♪ ተመስገን እላለሁ መልሼ እንደገና ♪ ብዙ የሰው ፍጡር እንደዚህ ነውና አሀ አሄሄ አሀ አሀሀ እምህ አሄሄይ እምህ አሀሀ ሰው ጊዜ አይቶ የሚጥለኝ ♪ የታመነው የሚከዳኝ የሆንኩለት የማይሆነኝ ሁልጊዜ የሚመሽብኝ አሀሀሀሀ አወይ ሰው መሆኔ ♪ አማርረውና አምላኬን በፀና ተመስገን እላለሁ መልሼ እንደገና አማርረውና አምላኬን በፀና ተመስገን እላለሁ መልሼ እንደገና እንደገና እንደገና እንደገና እንደገና
Audio Features
Song Details
- Duration
- 07:20
- Key
- 10
- Tempo
- 118 BPM