Lela Alayim

Lyrics

ስሙን እያነሳው የማጫውታችሁ
 ቆንጆ ነው ያሳሳል ብዬ የምላችሁ
 የተረታሁለት ሸጋ ይኸውላችሁ
 የተረታሁለት ሸጋ ይኸውላችሁ
 አያወራርድም አይኑማ ልዩ ነው
 እንግዲ ፍረዱኝ እንግዲ ፍረዱኝ ፍቅርዬ ይሄው ነው
 አይደለም ወይ በእውነት ጥርሱ የሚደነቅ
 አይቶ እያሳሳቀ አይቶ እያሳሳቀ እያለ ፍልቅልቅ
 ብቻዬን ብቻዬን ብቻዬን ብቻዬን
 ስተክዝ አይተው የታዘቡኝን
 ፍቅር ፍቅር ፍቅር ፍቅር
 ትቷታል እያሉ የሚያሙኝን
 ይሄን ልጅ ይሄን ልጅ ይሄን ልጅ ይሄን ልጅ
 ወድጄው እንደሆን ይወቁት
 ሌላ አላይም ሌላ አላይም ሌላ አላይም ሌላ አላይም
 ብዬ ለሰው የነገርኩት
 ስሙን እያነሳው የማጫውታቹ
 ቆንጆ ነው ያሳሳል ብዬ የምላቹ
 የተረታሁለት ሸጋ ይኸውላቹ
 የተረታሁለት ሸጋ ይኸውላቹ
 ፍቅርማ ፍቅር ነው እንኳን በሱ መቶ
 ያስጨንቅ የለም ወይ ያስጨንቅ የለም ወይ ልብን ናፍቆት ሞልቶ
 ሲራመድ እዩና ካላፈዘዛችሁ
 ውሸት ነው ማድነቄ ውሸት ነው ማድነቄ እኔው ልግረማችሁ
 ብቻዬን ብቻዬን ብቻዬን ብቻዬን
 ስተክዝ አይተው የታዘቡኝን
 ፍቅር ፍቅር ፍቅር ፍቅር
 ትቷታል እያሉ የሚያሙኝን
 ይሄን ልጅ ይሄን ልጅ ይሄን ልጅ ይሄን ልጅ
 ወድጄው እንደሆን ይወቁት
 ሌላ አላይም ሌላ አላይም ሌላ አላይም ሌላ አላይም
 ብዬ ለሰው የነገርኩት
 ሌላ ሌላ ሌላ አላይም ባይኔ ሌላ 'ላይም ባይኔ
 ሌላ 'ላይም ባይኔ ሌላ 'ላይም ባይኔ 'ላይም ባይኔ
 ሌላ 'ላይም ባይኔ ሌላ 'ላይም ባይኔ 'ላይም ባይኔ
 

Audio Features

Song Details

Duration
06:46
Key
10
Tempo
81 BPM

Share

More Songs by Aster Aweke

Albums by Aster Aweke

Similar Songs